የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ እና የሸገር ከተማ ትራንስፖርት ጽ/ቤት የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማሻሻል በቅንጅት መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

AMN – ታኅሣሥ 14/2017 ዓ.ም

በቢሮ ሀላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው አዲስ አበባ ከተማ በስራ ምክንያት በርካታ ሰዎች ወደ ከተማዋ የሚገቡና የሚወጡ ከመሆኑ አንፃር ከአዋሳኝ ከተሞች ጋር በጋራ መስራት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በስምምነቱ መሰረት የህዝብ ትራንስፖርቱ በምሽትም የተሳለጠ እንዲሆን የከተማ የህዝብ አውቶቡሶችን ጨምሮ የብዙሃን ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከርካሪዎች እስከ ምሽቱ አራት ሰአት ድረስ አገልግሎት እንዲሰጡ እንደሚደረግ ገልፀዋል።

የሸገር ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ መኮንን አምቤ በበኩላቸው በሁለቱ ከተሞች የተፈረመው የስምምነት ሰነድ የትራንስፖርት እንቅስቃሴውን እና የህዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከርካሪዎችን መቆጣጠር የሚያስችል እንደሆነ አንስተዋል።

በአሸናፊ በላይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review