የአፋር ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ተጠናቀቀ

You are currently viewing የአፋር ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ተጠናቀቀ

AMN- መስከረም 27/2017 ዓ.ም

ከመስከረም 21 ቀን እስከ መስከረም 27 ቀን ሲካሄድ በቆየው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ከ1ሺ 500 በላይ የወረዳ የማህበረሰብ ወኪሎችና የክልል ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

ሀገራዊ መግባባት ይፈጥራሉ የሀገርን ችግር ይቀርፋሉ የተባሉ አጀንዳዎች የተሰባሰቡበት የምክክር ምዕራፉ የተሰበሰቡ አጀንዳዎችንም ኮሚሽኑ ተረክቧል።

ለምክክር ጉባኤ የሚሳተፉ የክልሉ ተወካዮችም ተመርጠዋል።

ከእያንዳንዱ የማህበረሰብ ወኪልና የባለድርሻ አካላት ስድስት ስድስት ተወካዮች ተመርጠዋል።

አካታች ሀገራዊ ምክክር የሚደረግባቸው አሳታፊ አጀንዳዎች የተነሱበት የአጀንዳ የምክክር ምዕራፍ እንደነበርም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

የተመረጡ አጀንዳዎች ለኮሚሽኑ ምክር ቤት ይቀርባልም ተብሏል ።

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review