AMN- ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም
ታሪካዊው የ.ተ.መ.ድ. የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አፍሪካ አደራሽ ሕንጻ ዕድሳት ተጠናቆ ዛሬ ይመረቃል
የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሠረተበት እና የ.ተ.መ.ድ. የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ታሪካዊው አፍሪካ አዳራሽ የሚገኝበት ሕንጻ በ.ተ.መ.ድ. ጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ መሠረት የተካሄደው ሁሉን አቀፍ ዕድሳት ተጠናቆ ዛሬ እንደሚመረቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።