AMN – መጋቢት 3/2017 ዓ.ም
ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት የኩባ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ኤድዋርዶ ሮድሪጌዝ ፓሪያ በኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ፖርክ በመገኘት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል ።
የኢትዮጵያ እና ኩባ የሁለትዮሽ የዲፕሎማሲ ግንኘነት የተጀመረበትን 50ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ሚኒስትሩ በፖርኩ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የኢትዮጵያ እና የኩባ ወዳጅነት ዘመን ተሻጋሪ መሆኑን መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
በጉብኝቱ ወቅት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር አብርሃም መንግሥቱ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ፣የኢትዮጵያ እና የኩባ ህዝቦች ወዳጆች ማህበር አባላት እንዲሁም ትምህርታቸውን በኩባ የተከታተሉ የቀድሞ ተማሪዎች ተሳትፈዋል።