AMN – መስከረም 9/2017 ዓ.ም
የቀጣናውን የቱሪዝም ተወዳዳሪነት ማሳደግ፣ በሀገራቱ መካከል ያለውን የቱሪዝም ዘርፍ ትብብር ማጠናከር እና የቱሪዝም ምርት አማራጮችን ማስፋት ላይ ያተኮረ ነው::
የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) እንደገለፁት አባል ሀገራቱ በቀጣናዉ ያለዉን እምቅ የቱሪዝም ሀብት በተገቢዉ መንገድ ለመጠቀም በትብብር መስራት ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ እንደሆነ ገልፀዋል።
ዋና ፀሐፊው አክለውም የልማት እቅዱ በሀገራቱ መካከል ያለዉን የእርስ በእርስ ግንኙነት እና ትብብር በማጠናከር ዘላቂ የቱሪዘም ልማትን ለማረጋገጥ የሚረዳ መሆኑን ገልጸዋል።
የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያን በቱሪዝም ዘርፉ ተወዳዳሪ ለማድረግ ዓለም አቀፍ ደረጃቸዉን የጠበቁ የቱሪዘም መዳረሻ ስፍራዎች በስፋት እየሰራች መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ዛሬ ይፋ የተደረገዉ ማስተር ፕላንም የቱሪዝም ዘርፉን ሁለንተናዊ እድገት በዘላቂነት ለማረጋገጥ፤ በተበታተነ መልኩ የሚደረገውን ጥረት ወደ አንድ የሚያመጣ በመሆኑ ለእቅዱ ስኬት ኢትዮጵያ ጥረት እንደምታደርግም ገልጸዋል።
ማስተር ፕላኑ ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት የሚተገበር እንደሚሆንም ከቱሪዝም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
All reactions:
44