AMN ህዳር 20/2017 ዓ.ም
89ኛውን የምስረታ በዓሉን እያከበረ የሚገኘው የኢፌዴሪ አየር ኃይል አብራሪዎችን፣ ቴክኒሻኖችንና ዕጩ መኮንኖችን አስመረቀ።
በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የኢፌዲሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳን ጨምሮ የመከላከያ ከፍተኛ ጦር መኮንኖች፣ የአፍሪካ ሀገራት አየር ኃይሎች አዛዦች የሌሎች የፀጥታ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
“የተከበረች ሀገር የማይደፈር አየር ኃይል” በሚል መሪ ሀሳብ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የተመሰረተበት 89ኛ ዓመት በዓል እየተከበረ ነው።