የከተማ ኑሮና የግብርና ልማት መቀራረብ አስደናቂ ውጤት እያስገኘ መጥቷል-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት

You are currently viewing የከተማ ኑሮና የግብርና ልማት መቀራረብ አስደናቂ ውጤት እያስገኘ መጥቷል-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት

AMN – መስከረም 20/2017 ዓ.ም

የከተማ ኑሮና የግብርና ልማት መቀራረብ አስደናቂ ውጤት እያስገኘ መምጣቱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ትኩስ እና ጤናማ የሆኑ የጓሮ ተፈጥሯዊ ምግቦችን ለቤተሰብ ከማስገኘት ጀምሮ አዲስ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ እስከመሆን መድረሱ ተገልጿል።

የምግብ አቅርቦትን ማሻሻል ብቻ ሳይሆን የራሳችንን ኑሮ የተሻለ ለማድረግ፣ ጥቅም ላይ ያልዋሉ ቦታዎችን ወደበለጸጉ የአትክልት ስፍራዎች መለወጥ ብሎም የተተዉ ቦታዎችን ወደ ሀብት ማመንጫነት ለመቀየር እንደሚያስችል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review