የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሱፐርቪዥን ቡድን በአዲስ አበባ ሲያከናውን የቆየውን ምልከታ አጠናቀቀ

AMN – ታኅሣሥ 30/2017 ዓ.ም

በፌዴራል ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር የተቋቋመው የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት በአዲስ አበባ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ እና በክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ፅ/ቤቶች ሲያከናውን የነበረውን ሱፐርቪዥን በዛሬው እለት አጠናቀቀ።

ቡድኑ በእቅድ ዝግጅት፣ በይዘት ቀረፃ፣የሚዲያ ግንኙነት ፣የህዝብ ግንኙነት፣በዲጅታል ሚዲያ አጠቃቀምና ሞኒተሪንግ ዘርፍ እንዲሁም በጥናትና ምርምር ዘርፍን በአጠቃላይ በተቋሙ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ምልከታ አከናውኗል።

የፌዴራል ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እንዳልካቸው ፀጋዬ በምልከታቸዉ እንደተናገሩት ጠንካራ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራ ለሀገረ መንግስት ግንባታ ሚናው ላቅ ያለ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ከተማዋን በሚመጥን መልኩ ለሌሎችም ተሞክሮ መሆን የሚችል ሰፊ ስራዎች በአዲስ አበባ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መመልከታቸውንና ይህም ለሌሎች ክልሎች ጭምር ተሞክሮ ሊሰጥ በሚችል ደረጃ የተደራጀ የተግባቦት ሂደት መሆኑን ገልፀዋል።

የሱፐርቪዥኑ ቡድኑ አባላት በከተማ ፣ በክፍለ ከተማ እንዲሁም በሴክተር ተቋማት የጋራ የተቀናጀና የተናበበ የተግባቦት ተግባር እጅጉን መደሰታቸውን ጠቁመው ይህ ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመዋል።

ቡድኑ በአዲስ ከተማ ፣ የኮልፌ ቀራኒዮ እና የልደታ ክፍለ ከተማ የኮሙኒኬሽን ፅ/ቤቶች በመገኘት ሱፐርቪዥን ያካሄደ ሲሆን የጉለሌ ክፍለ ከተማ እስቱዲዮ ጉብኝትም ማካሄዱን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

+3

All reactions:

3434

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review