የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ አስደናቂ ክስተቶች

የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ አስደናቂ ክስተቶች

AMN – ጥር 26/2016 ዓ.ም

በኮት ዲቯር አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በተለያዩ አስደናቂ ክስተቶች የተሞላ ሆኖ ለግማሽ ፍፃሜ ደርሷል።

ከአስደናቂ ክስተቶቹ ጥቂቱን እንመልከት፦

👉🏽 የዋንጫው አዘጋጅ ሀገር ኮት ዲቯር ሁለት የምድብ ጨዋታዎችን በመሸነፏ ከወዲሁ ከውድድሩ ተሰናበተች ተብሎ ሲጠበቅ ምርጥ ሦስተኛ ሆነው ለጥሎ ማለፍ ጨዋታ ከሚያልፉ አራት ብሔራዊ ቡድኖች አራተኛዋ ለመሆን በቃች።

👉🏽 በመቀጠልም ሦስቱንም የምድብ ጨዋታዎች አሸንፋ ለጥሎ ማለፉ የደረሰችው ሴኔጋልን በመለያ ምት አሸንፋ ለሩብ ፍፃሜ ደረሰች።

👉🏽 በዚህም ሳያበቃ በሩብ ፍፃሜው ከማሊ ጋር ባደረገችው ጨዋታ ገና በመጀመሪያው አጋማሽ አንድ ሰው በቀይ ካርድ ወጥቶባት አብዛኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በጎዶሎ ሰው ተጫውታ፣ እስከ 90ኛው ደቂቃ 1 ለ 0 ስትመራ ቆይታ፣ አዲንግራ በ90ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ አቻ ሆና፣ ተጨማሪ 30 ደቂቃው አልቆ በ122ኛው ደቂቃ ላይ ዲያኪቴ ባስቆጠራት ግብ አሸንፋ በድራማዊ ክስተት ለግማሽ ፍፃሜው አለፈች! … ሙሉ መረጃውን ከፌስቡክ ገጻችን ያገኛሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review