AMN- መስከረም 22/2017 ዓ.ም
በለውጡ ኋላቀር የነበረውን አሰራር በመቀየር በአዲስ መልክ የተደራጀው የፖሊስ ጋራዥ የጥገና ማዕከሎች አቅማቸውን በማጎልበትና አሰራራቸውን ወደ ዲጅታል በማሳደግ የከባድና ቀላል ተሸከርካሪ መለዋወጫዎችን በራስ አቅም እያመረቱ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
ከዚህም ባለፈ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጨምሮ የሌሎች መስሪያ ቤት ተሸከርካሪዎችን ተቀብለው አስተማማኝ የጥገና አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ በጉብኝታቸው ወቅት ተመልክተዋል፡፡
ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ በለውጡ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሠራዊት የታጠቃቸውን የሎጂስቲክስ አቅሞችን በቅርበት እየተከታተሉ የጎደሉትንም በማሟላት አሁን ላይ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ የአንበሳውን ድርሻ እያበረከቱ እንደሚገኙ ተገልጿል።
ይህንኑ ተግባር የበለጠ አጠናክረው በማስቀጠል በ2022 በአፍሪካ ካሉ ምርጥ አምስት የፖሊስ ተቋማት ውስጥ የሚመደብ፤ ሙያዊ ብቃትን ያረጋገጠ፤ አካታች እና በሕዝብ ታማኝ የሆነ ዘመናዊ የፖሊስ አገልግሎት ተፈጥሮ ማየት የሚለው የተቋሙ ራዕይ ግቡን እንዲመታ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ሌት ተቀን በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየተጉ ይገኛሉ ተብሏል።
አሁን ላይም በርካታ አዳዲስ የአድማ ብተና እና ለግዳጅ አገልግሎት የሚውሉ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን ከውጭ ሀገር በግዥ እንዲገቡ በማድረግ የሠራዊቱን የግዳጅ አፈፃፀም አቅም በሎጀስቲክስ በማጠናከር ላይ እንደሚገኙ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።