የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ይሰጣል

AMN-ግንቦት 01/2017 ዓ.ም

የ2017 ትምህርት ዘመን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡

በወረቀት የሚፈተኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 21 እና 22/2017 ዓ.ም እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 29 እና 30/2017 ዓ.ም ወደሚፈተኑበት ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ ተገልጿል፡፡

በበይነ መረብ የሚፈተኑ ተፈታኞች ከመኖሪያ ቤታቸው በየቀኑ እየተመላለሱ በተመደቡበት መፈተኛ ማዕከል የሚፈተኑ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በፈተና ወቅት ለፈተና ስርቆትና ኩረጃ የሚውሉ ማንኛውንም ቁሳቁሶች መጠቀም የተከለከለ መሆኑንም የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review