ጀኔራል አበባው ታደሰ በደብረብርሃን የፊቤላ ኢንዱስትሪያል የመኪና መገጣጠሚያን ጎበኙ

You are currently viewing ጀኔራል አበባው ታደሰ በደብረብርሃን የፊቤላ ኢንዱስትሪያል የመኪና መገጣጠሚያን ጎበኙ

AMN – መስከረም 29/2017 ዓ.ም

የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ በደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኘውን ፊቤላ ኢንዱስትሪያል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የመኪና መገጣጠሚያን ጎብኝተዋል።

ጀኔራል አበባው ተገጣጥመዉ ለስራ ዝግጁ የሆኑ ተሽከርካሪዎችንና አጠቃላይ የኢንዱስትሪውን የስራ ሂደት ተዘዋውረዉ ተመልክተዋል፡፡

በጉብኝቱም የኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ሹማ አብደታ እና የአማራ ክልል የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊን ጨምሮ የክልሉ የዞንና የሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የፊቤላ እንዱስትሪያል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የመኪና መገጣጠሚያ ተመርቆ ስራ ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ መገለጹን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካው በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ጭምር እያመረተ የሚገኝና በሀገሪቱ ኢኮኖሚ የራሱን አሻራ ለማሳረፍ የተቋቋመ መሆኑን የፊቤላ ኢንዱስትሪያል የፕሮዳክሽንና ቴክኒክ ክፍል ሃላፊ አቶ ሳሙኤል ቀለመወርቅ ተናግረዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review