AMN – የካቲት 9/2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዌላ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በሂደት ላይ እንደምትገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኤክስ ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ከዋና ዳይሬክተሯ ጋር በነበራቸው ቆይታ የአባልነት ጥያቄው የደረሰበት ደረጃ ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል፡፡
የተደረገውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርም ተከትሎ ኢትዮጵያ ከሃገራዊ ጥቅሟ ጋር በሚጣጣም መልኩ ወደ አለም አቀፉ የንግድ ስርዓት እንድትቀላቀል ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።