ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኮይሻ ጊቤ የኃይል ማመንጫ ግድብ የሥራ ሂደትን ገመገሙ
AMN – ሐምሌ 20/2016 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለአስራ አራተኛ ጊዜ የኮይሻ ጊቤ 4 የኃይል ማመንጫ ግድብ ፕሮጀክት ስፍራ ተገኝተው የሥራውን ሂደት ገምግመዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ የኮይሻ ጊቤ 4 የኃይል ማመንጫ ግድብ ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቀጥሎ ትልቁ መሆኑን ገልጸዋል።
በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በፕሮጀክቱ በቀን እና በሌሊት በፈረቃ በመትጋት ላይ ይገኛሉም ብለዋል።
“ዛሬ ለአስራ አራተኛ ጊዜ በፕሮጀክት ስፍራው ተገኝቼ የሥራው ሂደት ገምግመናል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “ከስድስት ወራት በፊት ከነበረው ግምገማችን በኋላም ትርጉም ያለው እድገት መታየቱንም ተመልክተናል” ሲሉ ገልጸዋል።