ጤናማ አምራች ዘርፍን ከመፍጠር አንፃር ስፖርት የጎላ ሚና አለው – አቶ መላኩ አለበል

You are currently viewing ጤናማ አምራች ዘርፍን ከመፍጠር አንፃር ስፖርት የጎላ ሚና አለው – አቶ መላኩ አለበል

AMN-ሚያዚያ 19/2017 ዓ.ም

ጤናማ አምራች ዘርፍን ከመፍጠር አንፃር ስፖርት የጎላ ሚና ስላለው አምራች ኢንዱስትሪዎች ይህንን እሴት ለማሳዳግ ይረዳቸዋል ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገለጹ።

የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በመስቀል አደባባይ መካሄድ ጀምሯል ።

ታዋቂ እና አለም አቀፍ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የውጭ ሀገር ዜጎች፣ የተለያዩ ባለሙያዎች እንዲሁም የአምራች ኢንዱስትሪ ፋብሪካ ባለሙያዎች የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ላይ እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተጀመረ ወዲህ በተቋማት መካከል ቅንጅታዊ አሰራር እንዲፈጠር እና በዘርፉ የሚታዩ ማነቆዎች እንዲፈቱ ለማስቻል ጉልህ ሚና እንዳለው ተጠቁሟል።

መነሻ እና መዳረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው የኢትዮጵያ ታምርት የጎዳና ላይ ሩጫ፣ ከ1ኛ እስከ 10ኛ ለሚወጡ አሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት ይበረከትላቸዋል ተብሏል።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review