ለትራንስፖርት በዓመት ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ድጎማ እያቀረብን ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

You are currently viewing ለትራንስፖርት በዓመት ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ድጎማ እያቀረብን ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

AMN – ሚያዚያ 22/2017 ዓ.ም

ዛሬ በተካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ አመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከትራንስፖርት ጋር ተያይዞ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡

በከተማዋ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት ችግር ከመቅረፍ አንፃር በዓመት ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ድጎማ እያቀረብን ነው ብለዋል።

ሁል ጊዜም በተለመደ አሰራር ለውጥ ማምጣት አይቻልም ያሉት ከንቲባዋ በትራንስፖርቱ ዘርፍ የተለየ አሰራርን አስጀምረናል ብለዋል።

የትራንስፖርት ፍሰቱን የተቀላጠፈ ከማድረግ አኳያም ለአውቶቢስ አገልግሎቱ በመንግስትና የግል አጋርነት አዲስ የግል ቱር ኦፕሬተር ስራ መጀመሩን ገልጸዋል።

የከተማ አውቶቢሶችን በተመለከተም ለየት ባለ ዘመቻ ከዋናው መስሪያ ቤት እንዴት አገልግሎት እንስጥ በሚል ትልቅ ሪፎርም መደረጉን ገልፀው የአገልጋይነት መንፈስ እንዲዳብር ከፍተኛ ጥረት ተደርጓልም ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review