AMN – ጥር 16/2017 ዓ.ም
የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩናይትድ ስቴትስ አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ ጋር የኒዩክሌር መሳሪያ ቅነሳን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የስልክ ውይይት ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል።
ፔስኮቭ በሞስኮ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሩሲያ ለሚደረገው ውይይት የዋሽንግተንን ምላሽ እየጠበቀች ነው ብለዋል፡፡
የኒዩክሌር መሳሪያ ቅነሳን በተመለከተ፣ የዩናይትድ ስቴትስ አጋሮች የሆኑት ብሪታንያ እና ፈረንሳይን ከግምት ውስጥ ያስገባ ውይይት ለማድረግ ሩሲያ ፈቃደኛ መሆኗን ፔስኮቭ ማረጋገጣቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሩሲያ እና የዩክሬንን ጦርነት በፍጥነት ለማስቆም እንዲሁም የኒዩክሌር መሳሪያ ቅነሳን በተመለከተ ከሩሲያ አቻቸው ቭላዲሚር ፑቲን ጋር መነጋገር እንደሚፈልጉ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡