ሩሲያ የዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም ከአሜሪካ ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ ዝግጁ መሆኗን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ አስታውቀዋል።
ሚኒስትሩ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን ለማስቆም ሞስኮ እና ዋሺንግተን “በትክለኛ አቅጣጫ እየተጓዙ መሆኑን አምናለሁ” ብለዋል።
የዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ጦርነቱን ማስቆሚያ አይነተኛ ብልሃት ለመፈለግ ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር ለመምከር ሞስኮ እንደሚገቡ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡