AMN – የካቲት 16/2017 ዓ.ም
በሀረሪ ክልል “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሃሳብ የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ በተላለፉ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች እንዲሁም በልማት እና መልካም አስተዳደር ዙሪያ ላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ ህዝባዊ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ፣ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል፣ የአፋር ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ መሐመድ ሁሴን፣ የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ፣ የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሮዛ ኡመር ፣ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በኮንፈረንሱም ከህብረተሰቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች በፌደራል እና በክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።