በሀሰተኛ የተጭበረበረ ደረሰኝ መንግስት ሊያጣ የነበረውን ከ422 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን ተችሏል-አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

You are currently viewing በሀሰተኛ የተጭበረበረ ደረሰኝ መንግስት ሊያጣ የነበረውን ከ422 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን ተችሏል-አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

AMN-ጥር 18 / 2017 ዓ.ም

ባለፉት ስድስት ወራት በሀሰተኛ ደረሰኝ ግብይት ተጭበርብሮ ያለ አግባብ ሊቀር የነበረ ከ422 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳንና የመንግስትን ጥቅም ማስጠበቅ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ሕግ ተገዢነት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚኪያስ ሙሉጌታ እንደገለፁት፣ ባለፉት 6 ወራት በሀሰተኛ የተጭበረበረ ደረሰኝ መንግስት ሊያጣ የነበረው ከ422 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን ተችሏል።

ሀሰተኛ ደረሰኝ እንዲጣሩ ከቀረቡት አጠቃላይ 18 ሺ 542 ደረሰኞች 3 ሺ 301 ሀሰተኛ ሆነው ተገኝተዋል ብለዋል።

ሀሰተኛ ደረሰኞቹ የያዙት 422 ሚሊየን 848 ሺህ 248 ብር በመሆኑ ይህንን ማዳን መቻሉን አቶ ሚኪያስ አብራርተዋል።

በቀጣይ የበጀት ዐመቱ ቀሪ ወራት የታክስ ህግ ተገዢነትን ለማስፈንና ገቢን ለማላቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በትኩረት እንደሚሰራም አመላክተዋል ።

በአስመጪዎች፣ በአምራቾች ፣ በአከፋፋዮች እንዲሁም ቸርቻሪዎች ላይ የተጀመረው የታክስ ህግ ተገዢነት የማስፈን ተግባር በቀሪ ወራትም እንደሚጠናከር ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review