በሁሉም መልኩ ተከባብሮ በመኖር አብሮነታችንን ማጠናከር ይገባል-አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር

You are currently viewing በሁሉም መልኩ ተከባብሮ በመኖር አብሮነታችንን ማጠናከር ይገባል-አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር

AMN – መጋቢት 10/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር በተገኙበት ልዩ የኢፍጣር መርሃ ግብር በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ተካሂዷል።

በመርሐግብሩ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ሀገራችን ቅድስት ሀገር ናት፤ በሁሉም መልኩ ተከባብሮ በመኖር አብሮነታችንን ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡

የብዝሀነታችን መገለጫ የሆኑ ጉዳዮችን ምክንያት በማድረግ ሊለያዩን የሚሞክሩ አካላትን በጋራ በመታገል ህብረ ብሄራዊ አንድነታችንን ማጽናት ይገባናል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል::

የፌደራል ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ኘሬዝዳንት እና የፌደሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ዘሃራ ዑመድ የብልፅግና ፓርቲ ሰዉ ተኮር መገለጫ የሆኑት የመተባበር አብሮነት እህትማማችነት ይበልጥ በማጎልበት ያለንን ለሌሎች በማካፈል የጾሙን ወር ማሳለፍ ይገባል ብለዋል::

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል በበኩላቸው፤ የአብሮነት መገለጫዎቹ ታላቁ አንዋር እና ቅዱስ ራጉኤል ቤተ እምነቶች መገኛ ወደ ሆነው አዲስ ከተማ እንኳን በደህና መጣችሁ ማለታቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review