በኢራን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ መሐመድ ጋሊባፍ የተመራውን ልዑካን ቡድን የአድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኘ

You are currently viewing በኢራን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ መሐመድ ጋሊባፍ የተመራውን ልዑካን ቡድን የአድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኘ

AMN – ጥር 8/2017 ዓ.ም

በኢራን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ መሐመድ ጋሊባፍ የተመራው የልዑካን ቡድን በከሰዓት ውሎው የአድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኝቷል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት ኢትዮጵያ በልማት ጎዳና ላይ መሆኗን መረዳታቸውን እና በጉብኝቱም መደሰታቸውን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ ጥንታዊና ታሪካዊ ሀገር ናት ያሉት የልዑካን ቡድኑ አባላት በአድዋ ድል መታሰቢያ ካደረጉት ጉብኝት የኢትዮጵያውያንን አንድነት፣ አይበገሬነትና ጀግንነት መረዳታቸውን አብራርተዋል።

በተመሳሳይም በጉብኝቱ የኢትዮጵያን ታሪክ በመረዳታቸው እና ታሪካዊ ቁሳቁሶችን በማየታቸው መደሰታቸውንም ነው የልዑካን ቡድኑ አባላት የተናገሩት።

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የኢትዮ-ምዕራብ ኤዥያ የወዳጅነት ቡድን ሰብሳቢ የተከበሩ መሐመድ አሊ አል አሩሲ የኢራን ፓርላማ ልዑካን ቡድን ኢትዮጵያን ለመጎብኘት በመምጣቱ መደሰታቸውን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያና ኢራን ፓርላሜንታዊ ዲፕሎማሲ እንዲጠናከር እንደፓርላማ እንሰራለን ብለዋል።

ጉብኝቱም የኮሪደር ልማትን ጨምሮ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ለማስተዋወቅ እና የሀገሪቱን ገፅታ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለውም የተከበሩ መሐመድ አሊ አል አሩሲ ማስረዳታቸውን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review