በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነ የሰብዓዊ ትምህርት ቤት ተከፈተ

You are currently viewing በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነ የሰብዓዊ ትምህርት ቤት ተከፈተ

AMN – ጥር 19/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሰብዓዊ ትምህርት ቤት ማስጀመሪያ መርሀግብር እያካሄደ ነው።

ማህበሩ የሰብዓዊ ትምህርት ቤት ለማስጀመር ያስችለው ዘንድ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎቾንና ተቋማትን በማሳተፍ ጥናት ሲያካሂድ መቆየቱን ገልጿል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ማህበሩ በሀገሪቱ በተለያዩ ምክንያቶች ለተጎዱ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍን ከማድረጉ ባለፈ የትምህርት ተቋምን በመክፈት የሰብዓዊነት ጽንስ ሀሳብ በሳይንሳዊ መንገድ አስደግፎ ተደራሽ ማድረጉ ይበል የሚያሰኝ ነው ብለዋል።

ማህበሩ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ የመንግስት ድጋፍ እንደማይለየው ገልጸዋል።

ትምህርት ቤቱ በአዲስ አበባ ሳሪስ አካባቢ የተከፈተ ሲሆን አስፈላጊ ዝግጅቶች ተደርገው መጠናቀቃቸውንም የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ አበራ ቶራ ተናግረዋል።

ትምህርቱ የሚሰጠው በስቴሻል ዲፕሎማ ሲሆን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ሆኖ በሁለት ሴሚስቴር የሚሰጥ መሆኑንም ገልጸዋል።

ለትምህርቱ 9 የትምህርት ዓይነቶች የተዘጋጁ ሲሆን በበይነ መረብና በአካል ይሰጣል።

የሰብዓዊ ትምህቱን የሚሰጡ መምህራን የሀገሪቱን እሴት የሚያውቁና ሰብዓዊነትን የተረዱ ታላላቅ ሰዎች መዘጋጀታቸው የተገለጸ ሲሆን ትምህርቱን ለመማር ቢያንስ የማስተርስ ዲግሪ ያስፈልጋል ተብሏል።

በሄለን ጀንበሬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review