AMN- መስከረም 27/2017 ዓ.ም
በፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ምክር ቤቱ መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም ለሚያካሂደው 6ኛ የፓርላማ ዘመን 4ኛ የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ቀርበው በሚፀድቁ የውሳኔ ሃሳቦች ላይ እየመከረ ይገኛል፡፡
የቋሚ ኮሚቴውን ውይይት የመሩት የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሽመልስ አብዲሳ፤ ቋሚ ኮሚቴው በ2017 በጀት ዓመት የሚያከናውናቸው ዝርዝር ተግባራት የተካተቱበት ዕቅድ እንዲቀርብ በጠየቁት መሠረት የቋሚ ኮሚቴው ፀሐፊ አቶ ኃይሉ ኢፋ አቅርበው ሰፊ ወይይት ተደርጎበታል።
አቶ ሽመልስ አሁን በቋሚ ኮሚቴው አባላት የተሰጡ ግብዓቶች በጣም ጠቃሚዎች በመሆናቸው ለምክር ቤቱ በሚቀርበው የቋሚ ኮሚቴው የውሳኔ ሃሳብ ላይ እንዲካተት አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ያለፈውን የቋሚ ኮሚቴውን ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማፅደቁን የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡