AMN-መጋቢት 7/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን እየቀጣ ይገኛል።
በዛሬው እለትም በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት 4,505,000 / አራት ሚሊየን አምስት መቶ አምስት ሺህ/ ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡
ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በየካ ክፍለ ከተማ 3,740,000 ብር፤በአራዳ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር ፤በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 165,000ብር ቅጣት ቀጥቷል።

በአጠቃላይ በዛሬው እለት 10 ድርጅቶች እና 13 ግለሰቦችን በድምሩ 4,505,000 /አራት ሚሊየን አምስት መቶ አምስት ሺህ/ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን ባለስልጣኑ በማኅበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።
ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የሚበክሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
ህግ የማስከበሩ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።