ባለፉት ዘጠኝ ወራት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ያስከበሩ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራዎች ተከናውነዋል – ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)

You are currently viewing ባለፉት ዘጠኝ ወራት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ያስከበሩ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራዎች ተከናውነዋል – ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)

AMN – ሚያዝያ 06/2017

ባለፉት ዘጠኝ ወራት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ያስከበሩ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራዎች መሰራታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የ2017 በጀት ዓመት የሦስተኛው ሩብ ዓመት የ100 ቀን አፈጻጸም እና የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ትግበራ የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተገምግሟል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስም (ዶ/ር) የዲፕሎማሲ ዘርፉን አፈጻጸም አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ግንኙነቶች በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ በብሪክስ መድረክ ውጤታማ ተሳትፎ ማድረጓንም አመላክተዋል፡፡

በበጀት አመቱ ዘጠኝ ወራት ከአጎራባች ሀገራት ጋር ከወደብ እና የባህር በር ጉዳይ ጋር በተገናኘ የነበሩ አለመግባባቶችን በሰላማዊ ዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፈታታቸው፣ በኃይል መሰረተ ልማት ቀጣናውን ለማስተሳሰር ሰፋፊ ስራዎች መከናወናቸውንም ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review