ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር አብሮነትና አንድነትን የማፅናት እሴቶች የሚጎለብቱበት ነው ፦ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

You are currently viewing ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር አብሮነትና አንድነትን የማፅናት እሴቶች የሚጎለብቱበት ነው ፦ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

AMN-መጋቢት 6/2017 ዓ.ም

“ቁርአን የእውቀትና የሰላም ምንጭ” በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀው ሀገር አቀፍ የቁርአን ውድድርም ፍፃሜ በነገው እለት እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል።

ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር አብሮነትና አንድነትን የማፅናት ዓላማን እንደሚያሳካ ምክር ቤቱ ገልጿል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ዋና ኃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እንደገለፁት፤ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለቁርአን ልዩ ቦታ ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

ቁርአን የትውልድ የህይወት መርህና መመሪያ መሆኑን የገለፁት ኡስታዝ አቡበከር ይህንንም ከሁሉም በላይ ክብር ከፍ በማድረግ ትውልድን ለማነፃና ለማስተላለፍ ይገባል ብለዋል።

በዚህ የቁርአን ውድድር በሁለቱም ፆታዎች ፍፃሜ በአዲስ አበባ ይካሄዳል ብለዋል።

ሙስሊሙ ማህበረሰብ ቁርዓንን ከውድድር ባለፈ ሊኖረው እና የዕለት ከዕለት ህይወቱ መመሪያ ሊያደረገው እንደሚገባም ገልፀዋል።

ለውድድሩ አሸናፊዎች የኤሌትሪክ መኪና፣ የሃጅ ጉዞ ፣500 ሺህ እና 300 ሺህ ብር ሽልማት የሚበረከት መሆኑም ተገልጿል።

ከውድድሩ በተጨማሪ አምስተኛው የታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር የሚካሂድ መሆኑን አስታውቀው፤ የጋራ ሀገራዊ እሴት ከፍ ለማድረግ አብሮነትና አንድነትን የማፅናት አላማን የሚያሳካ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በመሀመድኑር ዓሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review