አርጀንቲናዊዉ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ከብሔራዊ ቡድኑ ውጪ ሆነ

You are currently viewing አርጀንቲናዊዉ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ከብሔራዊ ቡድኑ ውጪ ሆነ

AMN – መጋቢት 8/2017 ዓ.ም

አርጀንቲናዊው የቀድሞ የባርሴሎና ተጫዋች እና የአሁኑ የኢንተር ሚያሚ የፊት መስመር ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ መጠነኛ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገልጿል።

ጉዳት ማስተናገዱን ተከትሎ ሊዮኔል ሜሲ ዛሬ ይፋ በተደረገው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ ሳይካተት መቅረቱን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል፡፡

አርጀንቲና ከቀናት በኋላ ከብራዚል እና ዩራጓይ ጋር የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዋን ታደርጋለች፡፡

አርጀንቲና የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ምድቧን በ25 ነጥቦች እየመራች ትገኛለች።

የ37 አመቱ ሊዮኔል መሲ ለብሄራዊ ቡድን 191 ጨዋታዎች በማድረግ 112 ግቦችን ከመረብ ያሳረፈ ሲሆን 61 ኳሶችን አመቻችቶ ለቡድን አጋሮቹ ማቀበል ችሏል፡፡

የስምንት ጊዜ ባሎንዶር አሸናፊዉ ሜሲ፣ በትናንትናዉ ዕለት ለክለቡ ኢንተርሚያሚ ግብ ያስቆጠረ ሲሆን 2022 ኳታር ያዘጋጀችዉን የአለም ዋንጫ ከቡድን አጋሮቹ ጋር ማሳካቱ አይዘነጋም፡፡

በአዲሱ መንገሻ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review