AMN – የካቲት 25/2017 ዓ.ም
አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ገቢን ከማሳደግ ባሻገር የመንግስትን የውጪ ምንዛሬ ለማዳን ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ማዕከሉን የጎበኙ የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ማዕከሉ ለጉብኝዎች በይፋ ክፍት በሆነ በ 3 ቀናት ውስጥ በተለያዩ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ አካላት እና የከተማዋ ነዋሪዎች እየጎበኙት ነው።
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች፣ የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ሙሉ በሙሉ አግልግሎት መስጠት ሲጀምር ከዓለም ዳርቻ የሚመጡ አምራቾች እና አቅራቢዎች የሚገናኙበት ዋና መደረሻ እንደሚሆንም ገልፅዋል፡፡

የሀገሪቱን የኮንፈረንስ ቱሪዝም ከማሳደግ ባሻገር የመንግስትን የውጪ ምንዛሬ ፍላጎት ማሳደግ የሚያስችል ነው ሲሉም ተናግረዋል።
ሀገራችን ከተቀረዉ ዓለም ሀገራት ጋር የንግድ ስርዓቱን በማስተሳሰር የኢኮኖሚዉ ዘርፍ እንዲያድግ ከሰራቻቸዉ በርካታ ተግባራት አንዱ እና ዋነኛዉ የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ማሳያ መሆኑን በማንሳት በተሰራው ስራም የዜግነት ኩራት እንደተሰማቸው ገልጸዋል።
ለሀገር ዉስጥ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር እና የንግዱ ማህበረሰብም በሀገር ዉስጥ ንግድ ብቻ ሳይገደብ ከዓለም የንግድ ስርዓት ጋር ተቀላቅሎ ለመወዳደር ትልቅ ዕድል ይፈጥራል ሲሉም መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።