ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ96 ነጥብ 367 ሚሊየን ዶላር የድጋፍና ብድር ስምምነት ተፈራረሙ

You are currently viewing ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ96 ነጥብ 367 ሚሊየን ዶላር የድጋፍና ብድር ስምምነት ተፈራረሙ

AMN -መጋቢት 23/ 2017

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የትምህርት ዘርፉን ለማሻሻል የሚውል የ96 ነጥብ 367 ሚሊየን ዶላር ወይም የ12 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የድጋፍ እና ብድር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ እና በዓለም ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ማሪያም ሳሊም ተፈራርመዋል፡፡

ከተፈረመው ስምምነት ውስጥ 50 ሚሊየን ዶላሩ ከዓለም አቀፉ የልማት ማህበር በብድር መልክ የተሰጠ ሲሆን÷ 46 ነጥብ 367 ሚሊየን ዶላሩ ደግሞ ከዓለም አቀፉ የትምህርት አጋርነት ፈንድ በድጋፍ የተገኘ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ድጋፉ የቅድመ መደበኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትን ተደራሽ ለማድረግ የሚውል ነው መባሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review