ኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ያለው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ለአምራች ኢንዱስትሪው ምቹ የገበያ ዕድል የሚፈጥር ነው – አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ

AMN-ታህሳስ 7/2017 ዓም

የኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ያለው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ለአምራች ኢንዱስትሪው ምቹ የገበያ ዕድል መፍጠሩን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ ገለጹ።

ሚኒስትር ዴኤታው ከቻይና ሻንዶንግ ግዛት ምክትል ገዢ ሶንግ ጁኒል ጋር ተወያይተዋል።

በኢትዮጵያ ስላለው ሰፊ የኢንቨስትመንት እድል እና ለእርሻ ምቹ የሆነ መሬት ያላት እንዲሁም በተፈጥሮና በማዕድን የበለፀገች ሃገር ናት ሲሉ አቶ ታረቀኝ ገልጸዋል።

መንግስት ምቹ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ፣ የታክስ እፎይታ ፣ ከቀረጥ ነፃ ዕድል ፣ ለኢንቨስትመንት የተመቻቸ የአሰራር ስርዓት መዘርጋቱን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል፣ በግብርና ሜካናይዜሽን፣ በማኑፋክቸሪግ፣ በማዕድን እና በቱሪዝም ትልቅ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን ነው ሚኒስትር ዴኤታው የገለጹት።

ኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ያለው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ለኢንዱስትሪው እድገትና ምቹ የገበያ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን በማከል።

የቻይና ሻንዶንግ ግዛት ምክትል ገዢ ሶንግ ጁኒል ለኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ፣ በንግድ፣ በኢኮኖሚ፣ በቱሪዝምና በትምህርት ያለንን እውቀት ለማካፈል እንዲሁም በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ዝግጁ ነን ሲሉ መግለጻቸውንም ተመላክቷል።

በተያያዘም አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ እና የቻይናው ሻንዶግ ክፍለ ሃገር ምክትል ገዢ ሶንግ ጁኒል በሸገር ከተማ ሰበታ የሚገኘውን ውዳ ኢንዱስትሪል ግሩፕ ገብኝተዋል።

ኢንዱስትሪ ግሩፕ ወደ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ማደጉ ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ እድገት ሚናው ከፍተኛ እንደሆነ አቶ ታረቀኝ ገልጸዋል፡፡

ኢንዱስትሪ ፓርኩ ወደ ስራ ሲገባ ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ እና ዘርፈ ብዙ ምርቶችን የሚያመርት በመሆኑ የኢንዱስትሪውን እደገት የሚያሳይ እንደሆነም አክለዋል፡፡

ውዳ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሚያመርታቸው ምርቶች የብረት፣ የትራንስሚሽን ታውር፣ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ኬብሎች እና ባለሶስት እግር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ይጠቀሳሉ፡፡

ውዳ ኢንዱስትሪያል ግሩፕ በሸገር ከተማ ሰበታ የኢንዱስትሪ ፓርክ ለማቋቋም ወደ ስራ ለመግባት ሂደት ላይ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ኢንዱስትሪ ፓርኩ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ ለአስር ሺህ ሰዎች የስራ ዕድል የሚፈጥር ሲሆን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለማምረት ሂደት ላይ መሆኑን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review