ከለዉጡ በፊት በርካታ የለውጥ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም የመጋቢት 24/2010 ዓ.ም ለዉጥ በአይነቱ የተለየና የተሳካ ነዉ – አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

You are currently viewing ከለዉጡ በፊት በርካታ የለውጥ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም የመጋቢት 24/2010 ዓ.ም ለዉጥ በአይነቱ የተለየና የተሳካ ነዉ – አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

AMN – መጋቢት 24/2017

በኢትዮጵያ ከመጋቢት 24/2010 ዓ.ም የመጋቢት 24/2010 ዓ.ም በአይነቱ የተለየና የተሳካ ለውጥ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራርና አባላት መጋቢት 24 ሃገራዊ ለዉጡን ምክንያት በማድረግ ዉይይት አካሄደዋል፡፡ እለቱን በማስመልት በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በፖለቲካ በላፉት 7 ዓመታት የተገኙ ውጤቶች የመነሻ ሀሳብ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የብልጽግና ምክር ቤት አባል እና የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር በኢትዮጵያ ከመጋቢት 24/2010 ዓ.ም በፊት በርካታ የለውጥ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም የመጋቢት 24/2010 ዓ.ም በአይነቱ የተለየና የተሳካ ለውጥ መሆኑን በመጥቀስ ለውጡ ህዝባዊ፣ህገመንግስታዊ እና ድርጅታዊ እንዲሆን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር ) የለውጥ ሮድማፕ በማዘጋጀት ለለውጡ ስኬት የተወጡት ሚና በታሪክ የሚወደስ መሆኑን ገልጸዋል።

መጋቢት 24 በኢትዮጵያ ህዝቦች የመጣው ለውጥ ዘርፈ ብዙ ውጤቶችን ለኢትዮጵያና ለህዝቦችዋ አስገኝተዋል ያሉ ሲሆን ሀገራችን ከመበታተን አደጋ የታዳገ ለውጥ መሆኑን አውስተዋል ።

የብልጽግና ምክር ቤት አባል እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ሎሚ በዶ በበኩላቸው ለውጡ የኢትዮጵያን ህዝቦችን አንድነት ያጠናከረ፣ የህዝቦችን እኩል ተጠቃሚነትና የፖለቲካ ተሳትፎን ያረጋገጠ ቀን በመሆኑ እለቱን ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

በዲሞክራሲ ስርአት እና በተቋማት ግንባታ የመጣው ለውጥ ኢትዮጵያን በአለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተቀባይነት ያሳደገ እንደሆነ ጠቁመው መላው ህዝብ አሁንም ለውጡ የታለመለትን አላማ እንዲያሳካ ድጋፋቸውን አጠናክሮ መቀጠል አለባቸው ማለታቸዉን ከምክር ቤቱ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review