ስምምነቱ የተፈፀመው በቻይናዎቹ ሻንዥን ኢነርጂ ግሩፕ እንዲሁም በቻይና ብሔራዊ ኤሌክትሪክ ኢንጅነሪንግ ድርጅት እና በጀርመኑ ኮቬናንት ኢንጅነሪንግ ድርጅት መካከል ነዉ፡፡
የውል ስምምነቱ ረጲ አካባቢን ከቆሻሻ መድፊያነት ወደ ኢኮ ፓርክነት መቀየር የሚያስችል እና የሀይል አማራጭን በማስፋት ተጨማሪ የገቢ ምንጭ የሚያመጣ ስለመሆኑ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናግረዋል፡፡
ተቋማቱ ቆሻሻን ወደ ጥቅም እና ሀይል በመቀየር የካበተ ልምድ ያላችው መሆኑን ያነሱት ዋና ስራ አስኪያጁ ስምምነቱ ከተማዋን ውብ እና ፅዱ እንዲሁም ስማርት ሲቲ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡
የኮቬናንት ኢንጅነሪንግ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ቃልኪዳን ጋሻዉጤና በበኩላቸው ፤ ስምምነቱ ወደ ትግበራ ሲገባ ምቹ ስነ ምህዳርን ከመፍጠርም ባሻገር ለበርካታ ዜጎች የስራ እድልን የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በስምምነት መድረኩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታን ጨምሮ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሀይ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
በራሄል አበበ