ከ31 ሺህ በላይ የሁለተኛ ምዕራፍ የምግብ ዋስትና ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች ሽግግር በነገው ዕለት ይካሄዳል፡- ሥራና ክህሎት ቢሮ

You are currently viewing ከ31 ሺህ በላይ የሁለተኛ ምዕራፍ የምግብ ዋስትና ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች ሽግግር በነገው ዕለት ይካሄዳል፡- ሥራና ክህሎት ቢሮ

AMN – ታኅሣሥ 26/2017 ዓ.ም

በከተማ ልማታዊ ሴፍትኔትና የስራ ፕሮጀክት ወደ ዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ የተሻገሩ ከ31 ሺህ በላይ የሁለተኛ ምዕራፍ የምግብ ዋስትና ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች ሽግግር ሥነ ስርዓት በነገው ዕለት እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታውቋል።

በአዲስ አበባ በሁለተኛው ምዕራፍ የምግብ ዋስትና ፕሮጀክት ለታቀፉ ዜጎች ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ የገንዝብ ድጋፍ መደረጉን ቢሮው አስታውቋል።

በከተማ ልማታዊ ሴፍትኔትና የስራ ፕሮጀክት ወደ ዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ የተሻገሩ ከ31 ሺህ በላይ የሁለተኛ ምዕራፍ የምግብ ዋስትና ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች ሽግግር ሥነ ስርዓት በነገው ዕለት እንደሚካሄድም ቢሮው አስታውቋል።

በከተማዋ በድህነት በዝቅተኛ ገቢ ይተዳደሩ የነበሩ ወገኖች ላለፉት ሶስት ዓመታት በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ስራ ፕሮጀክት ታቅፈው ሲሰሩ መቆየታቸው ተነስቷል።

በፕሮጀክቱ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የተጋለጡ ወገኖች ከ2014 እስከ 2016 ዓ.ም በነበራቸው ቆይታ በልማት ስራዎች ላይ ተሰማርተው ወርሃዊ ክፍያ ሲያገኙ ቆይተዋል።

ተጠቃሚዎችም ከሚያገኙት ገንዘብ 20 በመቶውን በመቆጠብ ተቀማጭ የተደረገላቸው መሆኑን በማመላከት በፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ላይ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል ብለዋል።

የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች በዘላቂነት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር በተደረገው ጥረት የሕይወት ክህሎትና ገንዘብ አጠቃቀም ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉም ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ገቢ ማስገኛ ስራዎች፣ የንግድ ክህሎት ስራ ዕቅድ አዘገጃጀትን ጨምሮ የቴክኒክ ክህሎት ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉም ነው ቢሮው በመግለጫው ያስታወቀው።

በነገው እለትም ”ከተረጂነት ወደ ምርታማነት” በሚል መሪ ሃሳብ የሽግግር መርሃ ግብሩ የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review