ኪነ- ጥበብን ለሀገራዊ አንድነትና ብልፅግና በመጠቀም የአዲስ አበባን ልማት ማረጋገጥ ይገባል፡- አቶ ሞገስ ባልቻ

You are currently viewing ኪነ- ጥበብን ለሀገራዊ አንድነትና ብልፅግና በመጠቀም የአዲስ አበባን ልማት ማረጋገጥ ይገባል፡- አቶ ሞገስ ባልቻ

AMN – ታኅሣሥ 2/2017 ዓ.ም

ኪነ- ጥበብን ለሀገራዊ አንድነትና ብልፅግና በመጠቀም የአዲስ አበባን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ገለጹ፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ”የወል እውነት ለጠንካራ ህብረ-ብሄራዊነት ”በሚል መሪ ሀሳብ የፓርቲውን 5ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የኪነ- ጥበብ መርሃ-ግብር ተካሂዷል።

ኪነ ጥበብ ሀገራዊ አንድነት እንዲመጣ ፣ ጠላት ሀገርን ሲደፍር ህዝብን በማነቃቃት ጠላትን በማሳፈር ረገድ ትልቅ ሚና እንዳለው ይታወቃል፡፡

በመርሀ-ግብሩ ላይ አሁን ላይ የኢትዮጵያ ፈተና የሆነውን ድህነት ለማስወገድ እና ልማትን ለማረጋገጥ ዜጐች በአንድነት ለሀገራቸው ሰላምና ብልፅግና እንዲነሱ ማድረግ ይገባል ሲሉ አቶ ሞገስ ተናግረዋል፡፡

በመርሃ -ግበሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ባህል’ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች’ የክፍለ ከተማ አመራሮች እና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

በአንዋር አህመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review