ዛሬ ማለዳ በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የገነባነውን እና ለሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን የህጻናት የነርቭ እና ህብለሰረሰር ቀዶ ጥገና ህክምና የልህቀት ማዕከል አስመርቀናል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing ዛሬ ማለዳ በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የገነባነውን እና ለሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን የህጻናት የነርቭ እና ህብለሰረሰር ቀዶ ጥገና ህክምና የልህቀት ማዕከል አስመርቀናል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN-የካቲት 14/2017 ዓ.ም

ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች የተሟሉለት ይህ የልህቀት ማዕከል በዓመት ከአምስት ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ህጻናት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ለሀገራችን ህጻናት ትልቅ አስተዋፅዖ ያለው እንዲሁም ከተማችንን ህጻናትን ለማሳደግ ምርጥ አፍሪካዊት ከተማ ለማድረግ የጀመርነውን ስራ የሚደግፍ ነው።

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የተገልጋዮች ፍላጎት ለማስተናገድና በጤናው ዘርፍ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ትኩረት ሰጥተን በመስራት ላይ የምንገኝ ሲሆን፣ በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ለገነባነው ለዚህ የልህቀት ማዕከል የሪች አናዘር ፋውንዴሽን ላደረገልን አስተዋፅዖ በነዋሪዎቻችን እና በራሴ ስም ላመሰግን እወዳለሁ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review