የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ በ6 ወራት ውስጥ ከ12 ሚልየን ኩንታል በላይ ሲሚንቶ ለገበያ አቅርቧል

You are currently viewing የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ በ6 ወራት ውስጥ ከ12 ሚልየን ኩንታል በላይ ሲሚንቶ ለገበያ አቅርቧል

AMN- ሚያዝያ 16/2017 ዓ.ም

የኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ እና የዌስት ኢንተርናሽናል ሆልዲንግ ጥምረት የሆነው ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የማምረት ሂደቱን ከጀመረበት ከመስከረም 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 6 ወራት ከ12 ሚልየን ኩንታል በላይ ሲሚንቶ ለገበያ አቅርቧል፡፡

በቀን እሰከ 150 ሺህ ኩንታል ሲሚንቶን ማምረት የሚችለው የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ በኢትዮጵያ የሚገኙ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በድምር እያመረቱ ከሚገኙት ዓመታዊ የ 6.7 ሜትሪክ ቶን ላይ ለብቻው ከ4.5 ሜትሪክ ቶን በላይ ምርትን የማቅረብ አቅም እንዳለው ተነግሯል።

የሲሚንቶ ፋብሪካው የሀገራዊ የሲሚንቶ ፍላጎት እጥረትን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ የሚያስችል አቅም ያለው ሲሆን፣ ይህም በኢትዮጵያም ሆነ በምስራቅ አፍሪካ ግዙፉ የሲሚንቶ ፋብሪካ ያደርገዋል ተብሏል።

ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ በሲሚንቶ ምርት፣ በምርት ስርጭት እና ሌሎች የስራ ዘርፎች በሺህ ለሚቆጠሩ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩም ተገልጿል።

ፋብሪካው በአሁኑ ወቅት የኦፒሲ እና ፒፒሲ ምርቶች እያመረተምይገኛል።

የሚዲያ አካላትና የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችም የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካን ጎብኝተዋል።

በንጉሱ በቃሉ እና በወንድምአገኝ አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review