የምክር ቤት አባላት ቡድን በአፋር ክልል በርዕደ መሬት የተጎዱ ዜጎችን ጎበኘ

You are currently viewing የምክር ቤት አባላት ቡድን በአፋር ክልል በርዕደ መሬት የተጎዱ ዜጎችን ጎበኘ

AMN- ጥር 13/2017 ዓ.ም

ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተወጣጣ የምክር ቤት አባላት ቡድን በአፋር ክልል በርዕደ መሬት የተጎዱ ዜጎች ያሉበትን ሁኔታ ተመልክቷል።

ምልከታውን ያደረገው ከምክር ቤቱ የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ውጭ ግንኙነት እና የሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የተወጣጣ ቡድን መሆኑ ተገልጿል።

ቡድኑ በክልሉ በተከሰተው ርዕደ መሬት የተጓዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ያለው ጥረት መቀጠል እንዳለበት ገልጿል።

ከሰብዓዊ እርዳታ ጋር በተያያዘ የመጠለያ፣ የምግብና ውሃ አቅርቦት እንዲሁም የጤና አገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል እንደሚገባው አመላክቷል።

ለዜጎች የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር የክልሉ አመራሮች ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው በቁርጠኝነት እንዲሰሩ ማሳሰባቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review