የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አለህ መልእክት አስተላለፉ

You are currently viewing የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አለህ መልእክት አስተላለፉ

AMN – ጥር 12/2017

ለ2ተኛ ጊዜ ለተመረጡት 47 ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ለካቢኔ አባላቶቻቸው ከሩሲያ ጋር ግንኙነታቸውን ወደነበረበት ለመመለስ ፍላጎት እንዳላቸውም ተናግሯል፡፡

ዛሬ ማምሻውን በዋይት ሀውስ በተደረገ ስነስርአት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በአለ ሲመት ተከናውኗል፡፡

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለ ዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አለህ መልእክት በማስተላለፍ ሩሲያ በዩክሬን ጉዳይ ላይ ለመነጋገር በሯ ክፍት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዩክሬን ጉዳይ ላይ ከአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ጋር ለመነጋገር ዝግጁነታቸውን ፑቲን ገለፀዋል።

ፑቲን ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ በ2024 የተቃጡባቸውን ሁለት የግድያ ሙከራዎችን ጨምሮ የትራምፕን ዘመቻ ለነጩ ቤተመንግስት ማመናቸው ተገለጸ፡፡

ፑቲን ሀገራቸው ከአሜሪካ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗንም አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

ትራምፕ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ከፑቲን እና ከቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር ለመነጋገር ፕሮግራም መያዛቸውን ፎክስ ኒውስ አመልክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review