የሶማሊያ ፌዴራል ፓርላማ አባላት ሀገራችን መስቀለኛ መንገድ ላይ ናት አሉ

AMN ህዳር 18/2017 ዓ .ም

የሶማሊያ ፌዴራል ፓርላማ አባላት ዛሬ በምክር ቤቱ የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት ተከትሎ ባወጡት መግለጫ መቀመጫውን ሞቃዲሾ ያደረገው የፌደራል መንግስት ሀገሪቱን መምራት ያልቻለ አምባገነንና ግጭት ጠማቂ ሲሉ ከሰውታል

ፌደራል መንግስቱ ፈላጭ ቆራጭ በመሆን፣ ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት መፈፀሙንና ሠራዊቱንም አላግባብ ለፖለቲካ ጥቅም ማዋሉን እንዲሁም የዳኝነት አካሉ በፖለቲከኞች ተፅእኖ ስር መውደቁን አመልክተዋል ፡፡

በሀገሪቱ እየተንሰራፋ በመጣው ስርዓት አልበኝነት ህዝቡ በመንግስት ላይ ያለው እምነት እንዲሸረሸርና በጎሳ እንዲከፋፈል ምክንያት ሆኗልም ብለዋል ፡፤

በፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ እና በጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ አብዲ የሚመራው መንግስት ደካማ ሀገሪቱን ለመምራት አቅም እንዳነሰው በዚህም ዘረፋና የዜጎች መፈናቀል እንዲባባስ ማድረጉን አባላቱ በመግለጫቸውጠቁመዋል ፡፡

ከዚህ በመነሳትም የምክር ቤት አባላቱ ለፌደራል መንግስት የ”አንድ ሰው አንድ ድምጽ” በሚል የሚደረገው ቅስቀሳ የፕሬዚዳንቱን የስልጣን ዘመን ለማራዘም ጁባላንድን ለማተራመስ የተያዘ እቅድ በመሆኑ እንዲቆም ፣ በጎሳ ላይ በመመስረት መንግስት የሚወስዳቸው እርምጃዎች የነበረውን መከፋፈ እንዲያገረሽ የሚያደርግ በመሆኑ እንዲቆም ፤መራዘሙም የሶማሊያን ሰላም ስለሚያናጋና እምነትን ስለሚያሳጣ እንዳይራዘም አሳስበዋል ፡፡

የሶማሊያ ብሔራዊ ጦርን መከፋፈል የመከላከያውን አቅም ስለሚያዳክም እንዲሁም አልሸባብን እንዲያንሰራራ ስለሚያደርግ ሀገሪቱንም አደጋ ላይ ስለሚጥል እንዲቆም ፣ የፍትህ አካላትን ለፖለቲካ ፍጆታ ከማዋል እንዲቆጠብና ከህገ መንግስቱ ውጪ የሆኑ ህጎች እንዲሻሩ ጠይቀዋል ፡፡

እነዚህ ተግባራት የሶማሊያን አንድነት፣ ደህንነት እና ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥሉ በመሆኑም መንግስት በተቋማት ውስጥ የሚደረጉ ጣልቃገብነቶችን እንዲያቆም እና ጊዜያዊ ህገ-መንግስቱን እንዲያከብር ፣ የወታደራዊ ሃይሎችን አላግባብ መጠቀም በማቆም አልሸባብን ለዋጋ እንደሚገባ እንዲሁም ከፋፋይ ስልቶችን ወደ ጎን በመተው ለሀገር አንድነትና ልማት እንዲሰራ የምክር ቤት አባላቱ አሳስበዋል

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review