የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ የማቋቋም ሂደት የተቋረጠው እኛው በፈጠርነው ትርምስ ምክንያት ነው- አቶ ጌታቸው ረዳ

You are currently viewing የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ የማቋቋም ሂደት የተቋረጠው እኛው በፈጠርነው ትርምስ ምክንያት ነው- አቶ ጌታቸው ረዳ

AMN – መጋቢት 4/2017 ዓ.ም

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ ክልላዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በፕሪቶሪያው ስምምነት የተስማማነው አንድ የመከላከያ ሰራዊት እንዲኖር ነው ብለዋል፡፡

ከስምምነቱ በኋላ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይሰራቸዋል ብለን ያሰቀመጥናቸው የሪፎርም ስራዎች ነበሩም ብለዋል፡፡

የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ ማስፈታት እና መልሶ ማቋቋም ሂደት ለማስቀጠል የፌዴራል መንግስት ኃላፊዎች በዛሬው ዕለት ወደ ክልሉ ሊጓዙ እንደነበር የገለጹት አቶ ጌታቸው በክልሉ ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ወደ ስፍራው መሄድ አለመቻላቸው የፌዴራል መንግስት ጥፋት አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

በ 10 ሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ህይወት የመመለስ ፍላጎት እንዳላቸው በመግለጽ ‘እኛው በፈጠርነው ትርምስ ምክንያት ነው የተቋረጠው’ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

‘በራሳችን ጥፋት የተፈጠረን ነገር ለፌዴራል መንግስት መስጠት ተገቢ አይደልም’ ሲሉም ተናግረዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review