የተቋማት የማስፈጸም አቅምን የሚያጎለብቱ በርካታ የጥናትና ምርምር ስራዎች ተሰርተዋል – የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ

You are currently viewing የተቋማት የማስፈጸም አቅምን የሚያጎለብቱ በርካታ የጥናትና ምርምር ስራዎች ተሰርተዋል – የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ

AMN – መጋቢት 27/2017

የተቋማት የመፈጸምና የማስፈጸም አቅምን ከፍ የሚያደርጉ የምርምርና የጥናት ስራዎችን መስራቱን የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ አስታውቋል፡፡

አካዳሚው 4ኛውን ከተማ አቀፍ የምርምርና ጥናት ኮንፈረንስ እያካሄደ ነው።

5 የጥናትና ምርምር ሀሳቦች የሚቀርቡበት ኮንፈረንሱ፣ “ችግር ፈች ጥናቶች ለከተማችን ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ ያለው።

የአካዳሚው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጣሰው ገብሬ በመክፈቻው ወቅት እንዳሉት፣ ከተማዋ የደረሰችበትን ደረጃ የሚመጥን የአመራር ልማትና የሰው ሀብት ማብቃት ላይ አካዳሚው እየሰራ ነው።

ይህንኑ አላማ ለማሳካትም አካዳሚው ለ35 ሺህ አመራሮችና ለ31 ሺህ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል ብለዋል።

በምርምር ዘርፍም የከተማዋን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን የሚያሳልጡ 44 ሳይንሳዊ የምርምርና ጥናት ስራዎችን አካዳሚው መስራቱን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።

እነዚህ የጥናትና ምርምር ግኝቶችም ለሚመለከታቸው አስፈጻሚ ተቋማት በመስጠት ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ እያገዘ መሆኑን ነው አካዳሚው የገለጸው።

በአራተኛው የምርምርና ጥናት ኮንፈረሰ ከሚቀርቡ ጥናቶች መካካልም የከተማ አመራር ውጤታማነት፣ የህብረተሰብ ተሳትፎ ተግባራት ስኬቶችና ተግዳሮቶች እንዲሁም የንግድ ማጭበርበር መንስኤዎችና በሸማቾች ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ ላይ ያተኮሩ የጥናት ርዕሶች ይገኙበታል።

በፈቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review