የነቀምት – አንገር ጉቲን – አንዶዴ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች አስተዳደር አስታውቋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ከ1.9 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተከናወነ የሚገኘው የመንገድ ግንባታው 86.1 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል፡፡
በፕሮጀክቱ እስካሁን 21 ኪ.ሜ የአስፋልት ንጣፍ፣ 25 ኪ.ሜ አፈር ቆረጣ እና ሙሌትን ጨምሮ በርካታ የኮንስትራክሽን ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡
የመንገዱን ግንባታ እና የቁጥጥር ሥራ ቾንግኪንግ ኢንተርናሽናል ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እና ሬናርዴት ዩናይትድ አማካሪ መሐንዲሶች በጥምረት እያከናወኑት ይገኛሉ፡፡
ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በአካባቢው ያለውን የትራንስፖርት ችግር እንደሚቀርፍም ከአስተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡