AMN- የካቲት 30/2017 ዓ.ም
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባባቂው የአርሰናል እና የማንችስተር ዩናይትድ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ።
ዛሬ ምሽት 1፡30 ላይ በኦልድትራፎርድ በተደረገው ጨዋታ ባለሜዳው ማንችስተር ዩናይትድ በብሩኖ ፈርናንዴዝ አማካይነት ቀዳሚ መሆን ቢችልም ከእረፍት መልስ ዴክለን ራይስ ባስቆጠራት ግብ መድፈኞቹ አቻ ሆነዋል።
ከእረፍት መልስ የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉት ዩናይትዶች ተጨማሪ የግብ አጋጣሚዎችን ቢያገኙም ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል።
ሁለቱ ክለቦች ባለፉት 30 አመታት 72 ግዜ የተገናኙ ሲሆን ማንችስተር ዩናይትድ 31 ግዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ይወስዳል።
አርሰናል ደግሞ 24 ግዜ ሲያሸንፍ በቀሪ 17 ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርተዋል።
በአልማዝ አዳነ