የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሻርጃ ከተማ አዲስ በረራ ሊጀምር ነው

You are currently viewing የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሻርጃ ከተማ አዲስ በረራ ሊጀምር ነው

AMN – መጋቢት 30/2017

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሻርጃ ከተማ ከግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ የበረራ አገልግሎት የሚጀምር መሆኑን አስታውቋል።

አየር መንገዱ በማህበራዊ የትስስር ገጹ ይፋ እንዳደረገው፣ አዲሱ በረራ አገልግሎት በሳምንት ለአራት ቀናት የሚደረግ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚጀምረው አዲስ የበረራ መስመር መንገደኞች በተቀላጠፈ የበረራ አማራጭ የደማቅ ባህልና ሰፊ ኢኮኖሚያዊ እድሎች ባለቤት ወደ ሆነችው ሻርጃ ከተማ በቀላሉ እንዲጓዙ እንደሚያስችልም ገልጿል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review