የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ ለ ሁለተኛ ዙር ውድድር ዛሬ ጅማሮውን ሲያደርግ ንብ ተጋጣሚውን አሸንፏል።

You are currently viewing የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ ለ ሁለተኛ ዙር ውድድር ዛሬ ጅማሮውን ሲያደርግ ንብ ተጋጣሚውን አሸንፏል።

AMN_የካቲት 13/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረጉ የሁለተኛ ዙር የመክፈቻ ጨዋታ ንብ የካ ክፍለ ከተማን 2 ለ1 አሸንፏል።

ለባለ ድሉ ክለብ ሻሂብ ሙሀመድ እና ኤፍሬም ሌጋሞ ለየካ ደግሞ ካሳሁን ሰቦቃ ኳስና መረብ ያገኛኙ ተጫዋቾች ናቸው።

በሌላ ጨዋታ ስልጤ ወራቤና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 2 አቻ ተለያይተዋል።

በተለይ በሁለተኛው አጋማሽ ጠንካራ ፉክክር በተስተዋለበት ጨዋታ ፉአድ ሙሀመድና ይታገሱ ማንዶዬ የስልጤን ኢዘዲን ጀማልና አንዋር ኑሪ ደግሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ግቦች አስገኝተዋል።

በጨዋታው የግቡ ባለቤት ፋአድ ሙሀመድ በቀጥታ ከሜዳ ወጥቷል።

መርሀ ግብሩ ነገ ሲቀጥል ሱሉልታ ክፍለ ከተማ ከሻሸመኔ ረፋድ 3:30 ሲል ጨዋታቸው ይጀምራል።

የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ 5:30 ሲል ሲጀምር መሪው ደሴ ከተማ በአንድ ነጥብ ዝቅ ብሎ 3ኛ ላይ ከሚገኘው ሀላባ ከተማ ጋር ይገናኛሉ።

ደሴ መሪነቱን ተማጠናከር ሀላባ ደግሞ መሪነቱን ለመረከብ የሚያደርጉት ፍልሚያ ትኩረት ስቧል።

በዮናስ ሞላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review