AMN – የካቲት 25/2017 ዓ.ም
በሁሉም ስፖርት አይነት ስኬታማ የሆኑ ስፖርተኞች የሚሸለሙበት የላውረስ አዋርድ በዚህ አመት ለ25ኛ ግዜ ይደረጋል።
በ7 አይነት ዘርፎች እውቅና በሚሰጥበት ሽልማት የጅምናስቲክ ተወዳዳሪዋ ሲሞን ባይልስ፣ ዋናተኛው ሊዮን መርቻንድ፣ አሜሪካዊው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ሊብሮን ጀምስ እና የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቹ ካርሎስ አልካሬዝ በእጩነት ከቀረቡት መካከል ናቸው።
በአትሌቲክስ ደግሞ ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ሲፋን ሀሰን፣ ኬንያዊቷ ፌዝ ኪፕየገን፣ ጁሊያን አልፍሬዝ፣ ሙንዶ ዱፕላንቲ እና ሌትሲል ቴቦጎ ተጠቃሽ ናቸው።
ባርሴሎና ሴቶች ቡድን፣ ሪያል ማድሪድ እና የስፔን ብሄራዊ ቡድን የዓመቱ ምርጥ ቡድን እጩዎች ውስጥ የተካተቱ ክለቦች መሆናቸውን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡
በአልማዝ አዳነ