AMN – የካቲት 24/2017 ዓ.ም
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አመራሮች እና አባላት እንዲሁም የተለያዩ ሲቪክ ማህበራት ተወካዮች የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎብኝተዋል::
ማዕከሉ ሀገራችንን በሚመጥን ደረጃ መሰራቱ እጅግ እንዳስደሰታቸው የገለጹት የፖለቲካ ፓርቲ የጋራ ምክር ቤት አመራሮቹ በቀጣይም እንዲህ ባሉ የሀገርን ገጽታ የሚገነቡ ስራዎች ላይ ከመንግስት ጎን በመቆም እንደሚሰሩ በጉብኝታቸው ወቅት መግለጻቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል::