የፖፕ ፍራንሲስ ስርዓተ ቀብር ነገ ይፈጸማል

You are currently viewing የፖፕ ፍራንሲስ ስርዓተ ቀብር ነገ ይፈጸማል

AMN – ሚያዚያ 17/2017

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ የቀብር ስነ ስርዓት ነገ እንደሚፈጸም ቫቲካን አስታወቀች።

በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በሚደረገው ስነ ስርዓት ላይ 50 የሀገራት መሪዎች እና 10 የተለያዩ ሀገራት ንጉሶች እንደሚገኙ የቫቲካን ኒውስ መረጃ ያመለክታል።

በአደባባዩ ከሚደረገው መርሃ ግብር በኋላ የፖፕ ፍራንሲስ ቀብር ሮም በሚገኘው ሳንታ ማሪያ ማጆሬ ቤተ ክርስቲያን (ባዚሊካ) ይፈጸማል።

ፖፕ ፍራንሲስ በቤተ ክርስቲያኗ የሚቀበሩት በህይወት እያሉ በተናገሩት ኑዛዜ አማካኝነት ነው።

የሊቀ ጳጳሱን አስክሬን በቅዱስ ጰጥሮስ መካነ መቃብር ለመሰናበት በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለሰዓታት በመሰለፍ ሽኝት አድርገዋል።

የሽኝት መርሃ ግብሩ እስከ ዛሬ ምሽት 3 ሶስት ሰዓት ድረስ ይከናወናል።

የፖፕ ፍራንሲስ ባደረባቸው ከፍተኛ የሳንባ ሕመም የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይተው በያዝነው ሳምንት ሰኞ በ88 ዓመታቸው በመኖሪያ ቤታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review