ፖሊስ የሰላማችን ዘብ የልማታችንም ኃይል ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ በዕውቀት፣ በክህሎት የዳበረና በሥነ-ምግባር የታነፀ ፖሊስ የመገንባት አካል የሆኑ የፖሊስ ሠራዊት አባላትን ዛሬ ማስመረቃቸውን አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ ታላቅነቷን የሚመጥን፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማቷን ከፀረ ሰላም ኃይሎች የሚጠብቅ አስተማማኝ የሰላም ዘብ የሆነ የፖሊስ ኃይል ገንብታለች ነው ያሉት።
“ዛሬ የተመረቃችሁ የፖሊስ አባላት ኢትዮጵያ ከእናንተ ብዙ እንደምትጠብቅ በመገንዘብ፣ ራሳችሁን በየጊዜው በዕውቀትና በክህሎት እያጎለበታችሁ ሀገርና ህዝብን በሙያ ሥነምግባር እንድታገለግሉ አደራ እላለሁ” በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
መንግሥትም ፖሊስን በቴክሎጂ ለማላቅ፣ በሥልጠና ለማዘመን፣ የሥራ ቦታዎችን ምቹ ለማድረግ የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።